ስለ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ቀንድ ከሌሎች የዜና ተቋማት የቅርብ ጊዜ ርዕሶች። እያንዳንዱ ዜና በዋናው አሳታሚ ድረ-ገጽ ላይ ይከፈታል።
ሁሉንም ቋንቋዎች አሳይርዕሶች እና አጫጭር ቅንጭቦች ወደ ዋናዎቹ አሳታሚዎች ይወስዳሉ። አዲስ ጋዜጣ ይህን የውጭ ይዘት አያዘጋጅም ወይም አያርምም።
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ታሪካዊ በደል እና የህልውና አጀንዳን አብሮ የያዘ የሀገራችን ፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የቁጭት ምንጭ የሆነ ምዕራፍ ነው። በዚህ ወሳኝ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ጥልቅ የሆነ ሕጋዊ እና ታሪካዊ ዳሰሳ ከሚያደርጉ ሥራዎች መካከል በታዋቂው ሕግ ባለሙያ በያዕቆብ ኃይለማርያም (ዶ/ር) «አሰብ የማን ናት?» በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሐፍ […] The post “አሰብ የማን ናት?” appeared first…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ጂኦፓርኮች ዝርዝር ውስጥ በማስመዝገብ የመጀመሪያዋን ታሪካዊ የጂኦፓርክ እውቅና አግኝታለች። በዩኔስኮ የተመዘገበው ይህ ልዩ የተፈጥሮ ሀብት የኢትዮጵያን ድንቅ የጂኦሎጂ ቅርስ እና ስትራቴጂካዊ የቱሪዝም መስህቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ በጎላ ሁኔታ የሚያስተዋውቅ ከፍተኛ ብሔራዊ ስኬት ነው። ይኸው…
AMN- ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዓለማየሁ አረዳ (ዶ/ር) የተጻፈውን “ምሉዕነት” የተሰኘ መጽሐፍ አድንቀዋል። መጽሐፉ የግለሰብን ውስጣዊ እድገት ከማኅበረሰብ ጥንካሬ ጋር በማገናኘት፤ አካታች ፖለቲካን፣ የጋራ ብልጽግናንና ባህላዊ ብዝሃነትን የሚያቀናጅ ጥልቅ ሐሳብ ያቀርባል። የሥራው ዋና መልዕክትም ልዩነታችንን የመለያየት ምክንያት ሳይሆን የጥንካሬ ምንጭ አድርገን፣ በመተማመን፣ በትብብርና…
ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 reliable news source in Ethiopia ፈር ቀዳጁ ንጉሠ ነገሥት፡ በትምህርት ብርሃንና በፕሬስ ሥርዓት ኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪኳን ስትጽፍና የሉዓላዊነቷን አጽናፍ በዲፕሎማሲና በዕውቀት ስትከልል፣ የዕድገቷ ማዕቀፎች የተገነቡት በጠንካራ የሰው ኃይል ማፍራትና መረጃን ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ ዓበይት ምሰሶዎች ላይ ነበር። ከእነዚህ ታሪካዊ ምዕራፎች መካከል ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ጥቅምት 23 ቀን 1923…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሞ ሕዝብ የገዳ ሥርዓት ማኅበራዊ ሕግና የሕይወት ፍልስፍና ብቻ ሳይሆን፣ ባህልን፣ ተፈጥሮንና የሴቶችን ሚና የሚያገናኝ የማንነት ምሰሶ ነው። በዚህ የባህል ዓለም ውስጥ አቴቴ የእምነትና የጸሎት ሥርዓት ብቻ ሳይሆን የሴቶች ድምፅ፣ የማኅበረሰብ አንድነትና የተፈጥሮ ምስጢር መገለጫ ሆና ትታያለች። የክረምቱ ጨለማ አልፎ በጸደይ ብርሃን መተካቱን ተከትሎ በአብዛኛው በመስከረም መጨረሻ […] The post “የጥቅምት…
AMN-ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎች በአካል ተገኝተን የተመለከትነው ስራ እጅግ አስደናቂ ነው ሲሉ በቅርቡ የተመረቀውን የወንዝ ዳርቻ ልማት አድንቀዋል። በቅርቡ የተጠናቀቀው ከቀጨኔ በአምባሳደር ኢሬቻ እስከ ባምቢስ የተዘረጋው የወንዝ ዳርቻ ልማት የሀገራችን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ ቲክቶከሮች ጎብኝተዋል። በቦታው ተገኝተው የተሰራውን ድንቅ ስራ የተመለከቱት እነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ ቲክቶከሮች ”በአካል ተገኝተን…
በሩሲያ ታሪክ ውስጥ በጣም ታዋቂው አፍሪካዊ ግለሰብ፣ የታላቁ ሩሲያዊ ገጣሚ አሌክሳንደር ፑሽኪን ቅድመ-አያት አብራም ጋኒባል (Abram Gannibal) ነው። አፍሪካዊው አብራም ጋኒባል በ18ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በታላቁ ጴጥሮስ ቤተ-መንግሥት ገባ፡፡ ንጉሡም የክርስትና አባቱ ሆነ፤ ለትምህርትም ወደ ፈረንሳይ ላከው። ጋኒባል የወታደራዊ ስልጠና ወስዶ ኢንጂነር በመሆን፣ በመጨረሻም እስከ ጄኔራልነት ማዕረግ ደረሰ። የታሪክ ተመራማሪዎች የትውልድ ቦታውን በተመለከተ…
AMN- ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ከኢትዮጵያዊ እና ሩሲያዊ ቤተሰቦች የተወለደውና በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አሻራ ያሳረፈው የቀድሞው የሙዚቃ ባለሙያ ነርሲስ ናልቫንዲያን መኖሪያና የቅርስ ቤት በሰላም ኢትዮጵያ አማካኝነት ታድሶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። በ1929 ዓ.ም የተገነባው ይህ ታሪካዊ የቅርስ ቤት በውስጡ የስዕል ማሳያ ጋለሪን፣ እንዲሁም ሌሎች የጥበብ ሥራዎች መለማመጃዎችን አካቶ ለባለሙያዎች ክፍት መደረጉን የሰላም ኢትዮጵያ ፕሮግራም […]…