ስለ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ቀንድ ከሌሎች የዜና ተቋማት የቅርብ ጊዜ ርዕሶች። እያንዳንዱ ዜና በዋናው አሳታሚ ድረ-ገጽ ላይ ይከፈታል።
ሁሉንም ቋንቋዎች አሳይርዕሶች እና አጫጭር ቅንጭቦች ወደ ዋናዎቹ አሳታሚዎች ይወስዳሉ። አዲስ ጋዜጣ ይህን የውጭ ይዘት አያዘጋጅም ወይም አያርምም።
የዋጋ ግሽበት በሚቀጥሉት ስድስት ወራት “በድርብ አሃዝ” ውስጥ ይቆያል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለጸ። በመስከረም 2019 የተመዘገበው 14.9 በመቶ የዋጋ ግሽበት ከማዕከላዊው ባንክ የነጠላ አሃዝ ግብ “ከፍ ያለ” እንደሆነም አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን የተመለከቱ አሃዞችን ይፋ ያደረገው፤ ሁለት ገለልተኛ ባለሙያዎችን ጨምሮ ስምንት አባላት ያሉት የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ካደረገው ስብሰባ በኋላ ነው። ዛሬ ማክሰኞ […]
AMN – ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም፥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከኖርዌይ፣ ከቻይና እና ከካሊፎርኒያ የቴክኖሎጂ ማዕከላት ጋር የተያያዘ ይመስል ይሆናል፤ ነገር ግን ይህን ለውጥ ከሌላው የዓለም ክፍል በበለጠ ፍጥነት እና ድፍረት እያንቀሳቀሰች ያለችው ኢትዮጵያ ናት ሲል ብሉምበርግ ዘግቧል። በመኪና ማምረት ዝና የሌላት ኢትዮጵያ፣ በድንገት የዓለምን ትኩረት የሳበ የፖሊሲ ውሳኔ አሳልፋለች። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) […] The post…
AMN – ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም ኢትዮጵያ ያላትን ግዙፍ የታዳሽ እና የአማራጭ ኢነርጂ ሀብት በተቀናጀ መልኩ በመጠቀም የኢኮኖሚ ዕድገቷን ከማፋጠን ባለፈ፣ ለአካባቢ ጥበቃ እና ለቀጣናዊ የኃይል ትስስር ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተች ትገኛለች። በውኃ፣ በንፋስ፣ በፀሐይ እና በምድር በእንፋሎት (ጂኦተርማል) ሀብቷ የምትታወቀው ኢትዮጵያ፣ የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በርካታ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን እውን አድርጋለች። እነዚህ የኃይል ምንጮች ለኢንዱስትሪ ፓርኮች […]…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአቪዬሽን ዘርፍ ከብሔራዊ ደኅንነታችን ጋር የተያያዘ ስትራቴጂያዊ ጉዳይ ነው አሉ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ሲሳይ ቶላ (ዶ/ር)። በአቪዬሽን ደኅንነት ዘርፍ ለተገኘው ስኬት የዕውቅናና የምስጋና መርሐ ግብር ተካሂዷል። ጀነራል ሲሳይ ቶላ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የአቪዬሽን ዘርፍ ከሀገራችን የኢኮኖሚ እድገት ቀጣይነት፣ ከዓለም-አቀፍ ግንኙነትና ከአየር ትራንስፖርት […]…
AMN-ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም አዲሰ አበባ ከተማ የብልጽግና ተምሳሌትነቷን እያረጋገጠች ፤ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት እውን እያደረገች፤ የከተሜነት ጉዞዋን እያፋጠነች ትገኛለች፡፡ ከተማዋ በመፍጠር እና መፍጠን መርህ በ24/7 የሥራ ባህልን በመተግበር፤ ለዜጎች የቤት ልማት አቅርቦትን ለማሳደግ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ላይ የአቅርቦት እና የአሰራር ለውጥ በማድረግና የተለያዩ ሞዳሊቲዎችን በመቅረጽ ፤በመንግስት እና በግል አጋርነት፤በበጎ-ፈቃድ፤በግል ባለሀብቶች፣…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ደቡብ ኮሪያ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ልማት 15 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በጀት መደበች፡፡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለዓለም የወደፊት ኢኮኖሚያዊ የበላይነት ዋና መሰረት እየሆነ በመምጣቱን ተከትሎ በርካታ ሀገራት ለቀጣዩ ትውልድ ዲጂታል መሠረተ ልማት ከፍተኛ በጀት እየመደቡ ይገኛሉ። ደቡብ ኮሪያም የመደበችው ይህ ከፍተኛ በጀት በሶስት ዋና ዋና የቴክኖሎጂ ሜጋ […] The post ደቡብ ኮሪያ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ልማት…
AMN- ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም አዲስ አበባ በተከታታይ እያገኘች ያለችው ዓለም አቀፍ ዕውቅና ለቱሪዝም ዘርፉ አዳዲስ ዕድሎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ የከተማዋ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገልጿል አዲስ አበባ በዘላቂና ሰው ተኮር የከተማ ልማት ሥራዎቿ በተከታታይ ዓለም አቀፍ ዕውቅና እያገኘች ትገኛለች። በትናንትናው ዕለት በ2026 የሻንሃይ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት ሽልማት (የሻንሃይ አዋርድ) አሸናፊ ከሆኑ አምስት ከተሞች አንዷ ሆና […] The post አዲስ አበባ…
AMN- ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም እውነተኛ ልማት የሚለካው የሰዎችን ሕይወት በምን ያህል ደረጃ እንደቀየረ በሚያሳየው ውጤት እንደሆነና ይህም በከተማዋ በተጨባጭ እየታየ መሆኑ ይገኛል፡፡ አዲስ አበባ ለልማት ፕሮጀክቶች መሬት ስታውል የዜጎቿን መብት፣ ጥቅምና የኑሮ ሁኔታ በማክበር ልማትን ከሰው ሕይወት ጋር አስተሳስራ እየሠራች ይገኛል፤ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ ነዋሪዎች መንደርም የዚህ አካሄድ ጉልህ ማሳያ ነው። የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ […] The post ልማት…
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን የክለቡ የበላይ አመራሮች እና ደጋፊዎቹ በተገኙበት በአሁኑ ሰዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል እያከናወነ ይገኛል። በዚህም መድረክ ላይ በኢትዮጵያ ክለቦች ታሪክ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ መጠን… The post ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአጋር ድርጅቶቹ ከፍተኛ የተባለ ገንዘብ አገኘ appeared first on ሶከር ኢትዮጵያ.
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን የክለቡ የበላይ አመራሮች እና ደጋፊዎቹ በተገኙበት በአሁኑ ሰዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል እያከናወነ ይገኛል። በዚህም መድረክ ላይ በኢትዮጵያ ክለቦች ታሪክ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ መጠን… The post ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአጋር ድርጅቶቹ ከፍተኛ ገንዘብ አገኘ appeared first on ሶከር ኢትዮጵያ.
AMN- ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች አገራት ከተሞችም ጭምር አርዓያ እየሆኑ ይገኛል፡፡ ከተማዋ በቅርብ ዓመታት ያከናወነችው ፈጣንና ዘመናዊ የኮሪደር ልማት፣ የሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የነዋሪዎችን ኑሮ የሚያሻሽሉ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝተዋል፡፡ የአዲስ አበባ የከተማ ልማት ለውጥ የመንገድና የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ የወንዝ ዳርቻዎች…
AMN- ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም በኢትዮጵያና በጅቡቲ ኮሪደር ላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ኔትወርክ ለመዘርጋት ከሶስት የውጭ ኩባንያዎች ጋር የጋራ ኢንቨስትመንት ስምምነት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ-ጅቡቲ የትራንስፖርት መስመር ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ መሙያ አውታር ለመዘርጋት ከቻይና ሮድ ኤንድ ብሪጅ ኮርፖሬሽን፣…
AMN- ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም አዲስ አበባ ልማቷን ከነዋሪዎቿ ተጠቃሚነት ጋር በማቀናጀት ይህንን እውነታ በተግባር እያሳየች ትገኛለች። ይህም ጥረት ሌላ ዓለም አቀፍ ዕውቅና አስገኝቷል። በተባበሩት መንግሥታት የሰው ሰፈራ ፕሮግራም (UN-Habitat) እና በቻይና ትብብር በተዘጋጀው የ2026 የዓለም ከተሞች ቀን ላይ የሸንሃይ ሽልማት ከተቀበሉ ከተሞች መካከል አዲስ አበባ ተካትታለች። ይህ ዕውቅና ከተማዋ በሰው ተኮርና ዘላቂ ልማት የጀመረችውን ጉዞ […] The…
AMN- ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም ኢትዮጵያ የባህር በር ማጣቷ በሀገሪቱ የኑሮ ውድነት፣ የኢኮኖሚ ጫና እና የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደሩን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ነዋሪዎቹ ለ ኤ ኤም ኤን ዲስጂታል በሰጡት አስተያየት፤ የባህር በር ጥያቄ የትውልዱ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ የህልውና ጥያቄ መሆኑን አንስተዋል። የባህር በር ማጣት “የቤታችንን ደጃፍ መዝጋት ማለት ነው” ሲሉ የተናገሩት የአዲስ […] The post ቀይ ባህር ድሮም የኛ ነው ፤…
ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 reliable news source in Ethiopia ‹‹መንግሥት በዋናነት በአጭር ጊዜ የፖሊሲ ማስተካከያዎች ላይ ከመወጠር ኢኮኖሚውን የሚደግፉ መዋቅራዊ ችግሮችን ይፍታ›› አብዱልመናን መሐመድ (ዶ/ር)፣ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ባለሙያ አብዱልመናን መሐመድ (ዶ/ር) በሒሳብ አያያዝ፣ በኦዲትና በፋይናንስ አስተዳደር ዘርፎች ሰፊ ሙያዊ ልምድ ያካበቱ ኢትዮጵያዊ የፋይናንስ ተንታኝና ትንታኔያዊ ጽሑፎችን የሚያቀርቡ ባለሙያ…
ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 reliable news source in Ethiopia በለጋሾች የሚጀመሩ የግብርና መድን ፕሮግራሞች እንዳይከስሙ በመንግሥት አሠራር ውስጥ እንዲካተቱ ተጠየቀ በግብርናው ዘርፍ በለጋሾች ፈንድ የሚጀመሩ የመድን ፕሮጀክቶች የሙከራ ጊዜያቸው ሲያልቅ በመንግሥትና በባንኮች መደበኛ አሠራር ውስጥ ካልተካተቱ፣ የለጋሾች በጀት ሲያልቅ አብረው የመጥፋት ሥጋት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የልማት…
ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 reliable news source in Ethiopia በኢትዮጵያ የማገዶ እንጨት ለመልቀም በዓመት 20 ቢሊዮን ሰዓታት እንደሚጠፉ ተነገረ በዓመት ከ60 ሺሕ በላይ ሰዎች በእንጨትና በከሰል ምክንያት ሕይወታቸውን ያጣሉ ተብሏል በኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ የማገዶ እንጨት ለመልቀም በዓመት 20 ቢሊዮን ሰዓታት እንደሚጠፉ የዓለም ኢነርጂ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ የተጠቀሰው ሰዓት የቱኒዚያን ወይም የፖርቱጋልን አጠቃላይ…
ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 reliable news source in Ethiopia ስደተኞች በግል ሥራዎች እንዲሳተፉ የሚፈቅዱ የሕግ ማዕቀፎች ቢኖሩም የግንዛቤ ችግር መኖሩ ተገለጸ ስደተኞች ሊሰማሩባቸው የሚችሉ በሕግ የተደነገጉ የግል ዘርፎች ቢኖሩም፣ ተግባራዊ ለማድረግ ግን የግንዛቤ ችግር መኖሩ ተገለጸ። ኢትዯጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የስደተኞች ኤጀንሲ (UNHCR)፣ አማሆሮ ጥምረት (Amahoro Coalition) እና ኢንኮሞኮ…
ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 reliable news source in Ethiopia መንግሥት በበጀት ዓመት ከመድን ፈንድ 3.86 ቢሊዮን ብር መበደሩ ተነገረ የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ባለፉት አራት ወራት በሙዳራባህና በግምጃ ቤት ሰነድ ኢንቨስትመንት 3.86 ቢሊዮን ብር ለመንግሥት ማበደሩን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ፣ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘትና የገንዘብ አቅሙን ለማሳደግ፣ ፈንዱ በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ካሉ ከፍተኛ የአዕዋፍ ቱሪዝም አቅም ካላቸው ሀገራት አንዷ ናት አሉ በአእዋፍ ጥናትና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች፡፡ የአዕዋፍ ሳይንቲስትና የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ባለሙያው ይልማ ደለለኝ÷ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ከፍተኛ የአዕዋፍ ዝርያ ካላቸው ሀገራት በ4ተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ይናገራሉ፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ከ872 በላይ የአእዋፍ ዝርያዎች እንዳሉና ከነዚህ […] The post…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማ ልማት ስኬት የሚለካው ከዘመናዊ ሕንፃዎችና መንገዶች ባሻገር ለነዋሪዎች በሚፈጥረው ምቹ የመኖሪያ ከባቢ፣ በሚያስገኘው የኢኮኖሚ ዕድልና በሚያስመዘግበው ዘላቂ ልማት ጭምር ነው። ከዚህ አንጻር የአዲስ አበባ የከተማ ልማት ለውጥ የመንገድና የኮሪደር እንዲሁም የወንዝ ዳርቻዎች ልማት፣ የአረንጓዴ ስፍራዎች መስፋፋት፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የትራንስፖርት ተደራሽነት በዚህ […] The post…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁዋዌ የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይና ብሔራዊ የልማት ግቦቻችንን ለማሳካት በምናደርገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን በቅርቡ ስራ ከጀመሩት ኤሪክ ዩዋን ጋር ተወያይተዋል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ጉዞ ከሁዋዌ ጋር በትብብር፣ በብሔራዊ ባለቤትነት፣ በዘላቂነት፣ […] The post…
AMN- ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ፣ ቢሾፍቱ ፣ አዳማ ፣ ባቱ፣ ሞጆ እና ሐዋሳ ከተሞች ያስገነባቸውን 11 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ማቻረጃ ጣቢያዎች አስመረቀ። በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው የምረቃ ሥነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው ፤ የመሠረተ ልማት ምረቃው ኢትዮጵያ ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የምታደርገውን ስኬታማ ሽግግር የሚያሳይ መሆኑን […] The post…
AMN-ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም በመደመር መንግስት ዕይታ የከተማ ልማት ያሉንን የተፈጥሮ ፀጋዎች፣ የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ አቅም በማቀናጀት የነዋሪዎችን ሕይወት ማሻሻል፣ የከተማን ወጪ መቀነስና ዘላቂ ብልፅግናን ማረጋገጥ ነው። ትናንት የመጀመሪያዎቹ 26 የከተማ አውቶቡሶች በፊት ሲጠቀሙ የነበረውን የናፍጣ ነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ተቀይሮላው ሥራ መጀመራቸው ለሀገራችን እና ለመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ ከተራ የትራንስፖርት ሽግግር በላይ ትርጉም አለው። ይህ […] The…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ከሸሪዓ መርሆዎች ጋር የሚስማማ “ሚቹ-ሚዛን” የተሰኘ አዲስ የዲጂታል ፋይናንስ መተግበሪያ በዛሬው ዕለት አስመርቋል። በባንኩ የወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ኮፕባንክ አልሁዳ አማካኝነት የሚሰጠውና በክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ የሚደገፈው መተግበሪያው ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ንግዶች የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የታለመ ነው። በመደበኛ አገልግሎት ነጋዴዎች ከእምነታቸውና…
AMN- ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም የኢነርጂ ቅየራ ለትራንስፖርት አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችም ትልቅ አበርክቶ እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተለወጡ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ የኢነርጂ ቅየራ ሥራዎች የዜጎችን የኑሮ ጫና ለማቃለልና የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው አንስተዋል። የጋዝ ልማት ለኢንዱስትሪዎች…
AMN- ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም የመዲናዋን የትራንስፖርት አገልግሎት በጥራት፣ በብቃትና በዘመናዊ መልኩ ለማደራጀት ዘርፈ-ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት፣ የመጀመሪያዎቹን 26 ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተለወጡ አውቶብሶች ሥራ አስጀምረዋል፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ “የመዲናዋን የትራንስፖርት ችግር…
AMN-ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም በጥቂት ዓመታት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለውን የነዳጅ ተጠቃሚ አውቶብስ ሙሉ በሙሉ ወደ ጋዝ እንቀይራለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመጀመሪያዎቹን 26 ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተለወጡ አውቶብሶች ሥራ አስጀምረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት፤ ከጥቂት ወራት በፊት ጎዴ ላይ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ፌዝ የተፈጥሮ […] The post…
AMN- ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም የትራንስፖርት አገልግሎታችንን የበለጠ ፈጣን፣ ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ እንኳን ደስ አለን በማለት ዛሬ በአዲስ አበባ 26 የከተማ አውቶብሶችን ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ በመቀየር በጠቅላይ ሚኒስትራችን ሥራ አስጀምረናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ይህ ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነ ታላቅ […]…
AMN- ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመጀመሪያዎቹን 26 ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተለወጡ አውቶብሶች ሥራ አስጀምረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ዛሬ የመጀመሪያዎቹ 26 የከተማ አውቶብሶች ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ተለውጠው ሥራ ላይ በመዋላቸው የተሰማኝን ደስታ መግለጽ እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት የተፈጥሮ ጋዝ ምርትን ከሚመረትበት ስፍራ […] The…
AMN- ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም የ2018 የግብር ዘመን የደረጃ “ሀ” ዓመታዊ የንግድ ትርፍ የማሳወቂያና የመክፈያ ጊዜ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡ በዚህም ግብር ከፋዮች የመጨረሻ ቀናትን ሳይጠብቁ ግብራቸውን አሳውቀው በወቅቱ እንዲከፍሉ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል። የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለኤ ኤም ኤን እንደተናገሩት፤ የደረጃ ‹‹ሀ›› ግብር […] The post የ2018…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሩብ ዓመቱ ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ አረቦን ተሰብስቧል አለ የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ። ፈንዱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸሙን አስመልክቶ ለፋና ዲጂታል በላከው መግለጫ÷ አፈጻጸሙ ከዕቅዱ ጋር ሲነጻጸር የ100 በመቶ ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን አስታውቋል። ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ25 ነጥብ 48 […] The post በሩብ ዓመቱ ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር…
ሀገር በአንድ ጀምበር እና በአንድ ትውልድ አትገነባም፤ ሀገር መገንባት ውስብስብ ሂደት አለው፤ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ ወደ 400 የሚጠጉ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ አውቶቡሶች ይገባሉ፤ እነዚህ አውቶቡሶች እስኪገቡ ድረስም ነባር አውቶቡሶችን ወደ ጋዝ የመቀየር ሥራው ይቀጥላል፤ 400ዎቹ አውቶቡሶች ወደ አገልግሎት ሲገቡ፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙት የአንበሳ አውቶቡሶች ውስጥ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆኑት በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ ይሆናል፤ […] The post ጠቅላይ…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመዲናዋን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማዘመን ዘርፈ ብዙ ስራ እየተከናወነ ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡ ዛሬ የመጀመሪያዎቹ 26 የከተማ አውቶብሶች ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ተለውጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ሥራ ጀምረዋል፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የመዲናዋን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማዘመን ዘርፈ ብዙ […] The post…
AMN – ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ቀጠናዎች በፋርማሲዩቲካል እና በግብርና ማሽነሪ ማምረት ዘርፎች በጋራ የንግድ ሽርክና እንዲሰማሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻልና በግብርናው ዘርፍ ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየሰራች መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ትብብር በግብርና ማሽነሪዎችና ሰብል…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአባይ ተፋሰስን በተቀናጀ መንገድ ማልማት የኢትዮጵያን የኃይል ደህንነት ለማጠናከር ወሳኝ ነው አለ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፡፡ በ3ኛው የኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሳምንት የቀረበው ጥናት የአባይ ተፋሰስ ለውሃ፣ ለኃይልና ለምግብ ዋስትና በሚያበረክተው አስተዋጽኦ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ጥናቱን ያቀረቡት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሃይድሮሊክ ምህንድስና ተባባሪ አሰግድ ጋሻው (ፕ/ር) የአባይ ተፋሰስ ሰፊ […] The post…
AMN – ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ቀጠናዎች በፋርማሲዩቲካል እና በግብርና ማሽነሪ ማምረት ዘርፎች በጋራ የንግድ ሽርክና እንዲሰማሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻልና በግብርናው ዘርፍ ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየሰራች መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ትብብር በግብርና ማሽነሪዎችና ሰብል…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በተሳሳተ ደረሰኝ የሚከናወኑ የንግድ ማጭበርበሮችን መከላከል የሚያስችል ባለ ኪው አር ኮድ ምስጢራዊ የደረሰኝ ሕትመት ተጀምሯል። የባለ ኪው አር ኮድ (QR Code) ምስጢራዊ የደረሰኝ ሕትመት ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል። የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ጥላሁን ፈንታው በዚሁ ወቅት ፥ የሕትመት አሠራሩ ለዝግጅት […] The post በአማራ ክልል የንግድ ማጭበርበሮችን…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዔ ወደፊት ወደ አፍሪካ አህጉር በሚመጣበት ጊዜ የአፍሪካ ሕብረት መዲና የሆነችው አዲስ አበባ መድረኩን ለማስተናገድ ዝግጁ ናት አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ3ኛው ሩሲያ – አፍሪካ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ፥ አዲሱ የሁለትዮሽና የአህጉራዊ ትብብር የድርጊት መርሃ-ግብር ግልጽ ተግባራትንና የተወሰኑ የጊዜ ሰሌዳዎችን አካቶ መውጣት […] The post አዲስ አበባ…
AMN- ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም የ70 ግራም ዳቦ የመሸጫ ዋጋ 13 ብር እንዲሆን መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ ዳቦ አምራች ነጋዴዎች ማህበር አስታወቀ፡፡ የመሰረታዊ የፍጆታ ምርቶችን አቅርቦት በማብዛት በሻጭ እና በገዥ መካከል ጤናማ የንግድ ትስስር ለመፍጠር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ የዳቦ ጥራት፣ አቅርቦት እና ዋጋን ለማስተካከል የንግዱ ማህበረሰብ ሲመክር ቆይቶ፣ አሁን ላይ የ70 ግራም […] The post በአዲስ አበባ የ70…
AMN – ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሶስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች እንደምትገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላፉት መልዕክት ፣ በሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በመገኘት መልዕክቴን ማስተላለፍ በመቻሌ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል። በዚህ ታሪካዊ መድረክ የምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ተጨባጭ…
AMN – ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት አምስት ዓመታት የነዋሪዎችን መሰረታዊ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነውን የቤት ችግር በመረዳት አዲስ የለዉጥ እሳቤን እዉን በማድረግ 496ሺ 971 ቤቶች ተገንብተዉ ለነዋሪዎች እንዲተላለፉ አድርጓል:: ከተማ አስተዳደሩ በቤት ግንባታ ልማት ሂደት ዉስጥ የመንግስት ሚና ቀዳሚ በማድረግ የተለያዩ የግንባታ አማራጮችን በመዘርጋት ቤት አልሚ ሪል እስቴቶች፤ የግል አልሚዎች ህብረት […] The post…
AMN- ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊና የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በድጋሚ አረጋግጠዋል። ፕሬዚዳንቱ፣ እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ንግድ፣ እየሰፋ ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር እና በዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ተመሳሳይ አቋም አፅንኦት ሰጥተው ገልጸዋል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው ዘገባ፣ ፕሬዚዳንት ፑቲን […]…
AMN- ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም አዲስ አበባ የአፍሪካን አራተኛውን የግሉ ዘርፍ የመፈናቀል ፎረም ከኅዳር 7 እስከ 9 ቀን 2019 ዓ.ም ልታስተናግድ መሆኑ ተገለጸ። በፎረሙ ከንግዱ፣ ከመንግሥት፣ ከፋይናንስና ከሰብዓዊ ድጋፍ ዘርፎች የተውጣጡ ተወካዮችን እንዲሁም በመፈናቀል የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ይሳተፉበታል፡፡ የተፈናቀሉ ወገኖች በኢኮኖሚው ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ የሥራ ዕድልን፣ ኢንቨስትመንትንና የንግድ ሥራ ልማትን ማስፋፋት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በምግብ፣ በኃይል እና በእውቀት ላይ ኢንቨስት እያደረገች ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በሞስኮ እየተካሄደ ባለው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) በምግብ ረገድ ቀዳሚ ዓላማችን ሕዝባችንን መመገብ እና ለዘላቂ ብልጽግና የሚሆን የግብርና ኢኮኖሚ መገንባት ነው ብለዋል። […] The post በምግብ፣ በኃይል…
AMN- ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ውይይታችን በኒውክሊየር ኃይል፣ በጤናና ንግድ ዘርፎች ያለውን ትብብር እንዲሁም በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን…
AMN- ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም በ2019 በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ግብር ከፋዮች ሙሉ በሙሉ ዓመታዊ ገቢያቸውን በኦንላይን የሚያሳውቁበትና ግብራቸውን የሚከፍሉበትን አሰራር እውን ማድረጉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡ ቢሮው ከ2019 በጀት አመት ጀምሮ የግብር አሰባሰብ አሰራሩን በኦንላይን ማድረጉንና በደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች የሚነሱ ቅሬታዎችንና ለብልሹ አሠራር ሊዳርጉ የሚችሉ ጉዳዮችን ለመቅረፍ 24 አዳዲስ አሠራሮች በመዘርጋት ወደ ተግባር […] The…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሠራተኞችን የጡረታ ቁጠባ በጥብቅ ቁጥጥር፣ በግልጽነት እና በጥንቃቄ በተሞላ የኢንቨስትመንት አስተዳደር እና በጠንካራ የቁጥጥር ሥርዓት መጠበቅ ይገባል አሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)። የአፍሪካ የመጀመሪያው “የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓቶችን ማቀናጀት ለአፍሪካ የመሠረተ ልማት እና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የአፍሪካ ማህበራዊ ዋስትና ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ […] The…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያና ሩሲያ ስትራቴጂካዊ ትብብር የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ በእጅጉ የሚያፋጥን ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በመገኘት መልዕክቴን ማስተላለፍ በመቻሌ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል። በዚህ ታሪካዊ መድረክ የምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ተጨባጭ ውጤት እንዲያስመዘግቡ…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 ኤፍ ኤም ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በተመረቀው የመገጭ ግድብ የቆሮሶ ዝርያ ያላቸው 125 ሺህ የዓሳ ጫጩቶች ተጨምረዋል። የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ባለሙያ አቶ አበበ ፈንታሁን እንደገለጹት፤ ክልሉ ያለውን የዓሳ ሀብት ልማት ሰፊ አቅም ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም ያለውን የውሃ አማራጭ በመጠቀም የዓሳ ምርታማነትን ለማሳደግ […] The post 125 ሺህ የዓሳ ጫጩቶች ወደ…
AMN-ጥቅምት 18/2019ዓ.ም የመደመር መንግሥት መጽሐፍ እንደሚያብራራው፣ ልማት ማለት ከአካላዊ ግንባታ በላይ የሆነ፣ ሰውን ማዕከል ያደረገ፣ ሀብቶችን በተቀናጀ መንገድ የሚጠቀም፣ የሕዝብ ተሳትፎን የሚያጠናክርና የጋራ ብልጽግናን የሚያሳድግ ሂደት ነው። በዚህ እሳቤ መሠረት የከተማ ልማት መንገዶችን፣ ሕንፃዎችንና መሠረተ ልማቶችን ከመገንባት ባለፈ፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ አቅምን ማሳደግ፣ ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅና ለቀጣይ ትውልድ የሚተርፍ ዘላቂ…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በኢነርጂ ዘርፍ በተለይም የሰላማዊ ኒውክሌር ቴክኖሎጂ ልማት እና የቁጥጥር ማዕቀፎችን በመዘርጋት ረገድ የጠበቀ ትብብር እያደረጉ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ለኢነርጂ ዘርፍ ሰፊ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ሲሆን፤ ዘርፉ የሀገሪቱን አጠቃላይ ኢኮኖሚ፣ የኢንዱስትሪ ልማትና የቀጣናዊ የኃይል ትስስር ማጠናከሪያ ምሰሶ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይልን እንደ አማራጭ የኢነርጂ ዘርፍ ለመጠቀም […] The post…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ25 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል አለ የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ። የቢሮ ኃላፊ አሰለፈች መብራቱ እንደገለጹት ፥ በሩብ ዓመቱ ለ11 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ዕቅዱን በእጅጉ በማብለጥ 25 ሺህ 374 ወጣቶችን […] The post በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በሩብ ዓመቱ ከ25 ሺህ በላይ…